ህይወት ልክ እንደ ጠላ ነዉ ድፍድፉን ለይተህ ካላወጣህ የሚጣፍጠዉን ጠላ ማግኘት አትችልም ፡፡ አስተሳሰብህን መቀየር የምትችለዉ እና ተአምር እንደምትፈጥር የምታምነው መልካሙን ጓደኛ መለየት ሲቻልህ ነዉ፡፡
መልካም እና አስተዋይ ጓደኛ የህይወት ስንቅ ነዉ ከምሬት ወጥቼ አስተሳሰቤን እንዳዘምን ህልሜን እንድረዳ እና ለግብ እንድነሳ እንደ ገፀበረከት ከፈጣሪ የተሰጡኝ የጓደኞቼ ድጋፍ ህይወቴ ላይ ተአምር ፈጥሯል ፤ ስለዚህ ነዉ “ጓደኝነትህ ለአላማህ እንጂ አላማህ ለጓደኝነት አይሁን” የሚለዉ ድምፅ ሀይለኛ ስሜት የሚፈጥረዉ ፡፡
እኛም ለሌሎች መልካም አመለካከት ያለዉ ወይም ያላት ትዉልድ መሆን ከቻልን፤ እኛ ባወቅነዉ ልክ ጓደኛችንን ካሳወቅን ߹ እስከ ስኬት ጫፍ ድረስ ከተባበርን ߹ ህልማችንን ለማሳካት አብረን ከተጔዝን፡ ዘመናዊ አስተሳሰብን ለማሰፋፋት ከቻልን ህልም ያለዉ እዉነተኛ ጓደኛ መሆን እንችላለን፡፡