አንዳንድ ጊዜ አንድን ነገር ጀምረን ገና አንድ እርምጃ ሳንራመድ ውጣውረዶች በሕይወታችን ብቅ ማለት ይጀምራሉ፡፡ ይህ በሚሆንበት በሳልነታችን ወሳኝ ነው፡፡ በመንገዳችን ላይ በሚገጥሙን ውጣውረዶች በመጨናነቅ እነሱ እስከሚወገዱ ዓላማችን ይገታል ወይስ ውስጣችንን ሰፋ አድርገን ወደፊት እንገሰግሳለን?

በአመለካከታቸው የበሰሉ ሰዎች ከሌሎቹ የሚለዩት በጊዜያዊ ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ምክንያት ከዓላማቸው የአለመነቃነቃቸው ጽኑነት ነው፡፡ ይህን አይነቱ በሳልነት የሚመጣው የሚከተሉትን አውነታዎች በመገንዘብና በመለማመድ ነው፡፡

1. የተዛባውን አመለካከት ማስተካከል
በትንሹም በትልቁም ከዓላማቸው የሚመለሱ ሰዎች ቅን አመለካከትና ጥሩ ዓላማ እስከያዙ ድረስ ምንም እንቅፋት ሊገጥማቸው እንደማይችል የሚያስቡ ሰዎች ናቸው፡፡ በዓላማ ለመጽናት ግን ይህንን የተዛባ አመለካከት ማስተካከል የግድ ነው፡፡

2. የሁኔታዎችን ጊዜያዊነት መገንዘብ
እውነቱ አጭርና ግልጽ ነው! ማንኛውም የሚገጥመን ችግር እድሜው ውስን ነው፡፡ ቀድሞ የያዝነውን ጤናማና አዎንታዊ አመለካከት ሳንለቅ ጉዟችንን ከቀጠልን የጊዜው ሁኔታ ያልፋል እኛ ግን ዓላማችንን ይዘን እንቀጥላለን፡፡

3. የችግርን ጥቅም መገንዘብ
በምንም አይነት ችግር ውስጥ ስናልፍ ማስታወስ ያለብን፣ ሁኔታው ካለፈ በኋላ ከዚህ በፊት ያልነበረንን ጥንካሬን ይዘን፣ ከዚህ በፊት ተምረን የማናውቀውን ትምህርት አግኝተን እንዘልቃለን፡፡
Dr EYOB MAMO