ዝሆን እና ውሻ በተመሳሳይ ጊዜ ፀነሱ፡፡ ከሶስት ወራቶች በኋላ ውሻዋ ስድስት ቡችላዎችን ወለደች፡፡ ዝሆኗ እንዳረገዘች ከስድስት ወር በኋላ ውሻዋ እንደገና ፀነሰች ፣ ዘጠኝ ወር ደግሞ ሌሎች ብዙ ቡችሎች ወለደች፡፡ የእርግዝና ስርዓቱ ቀጠለ፡፡ ውሻዋ በየሦስት ወሩ መውለዷን ቀጠለች።

በአሥራ ስምንተኛው ወር ውሻዋ ወደ ዝሆኗ ጥያቄ ይዛ ቀረበች፤ “እርግጠኛ ነሽ ነፍሰ ጡር ነሽ? አሁን በሆድሽ ጽንስ አለ? ምክንያቱም በተመሳሳይ ቀን ነፍሰ ጡር ሆነናል ብለን ነበር፤ ከ16 በላይ ቡችሎች ወለድኩኝ እና አሁን ግማሾቹ በዚህ ሰዓት አድገው ትልቅ ውሾች ሆነዋል፤ ግን አንቺ አሁንም ነፍሰ ጡር ነኝ ትያለሽ፡፡ ምን እየሆነ ነው?”

ዝሆኗም “እኔ እንድትረጂ የምፈልገው አንድ ነገር አለ፤ በማህጸኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነው፡፡ እኔ በሁለት ዓመት ውስጥ አንድ ብቻ እወልዳለሁ፡፡ የምወልደው ግን ተራ እንስሳ ስላልሆነ ልጄ መሬቱን ሲመታ ምድር ይሰማታል ትርድዳለች ፡፡ ልጄ መንገዱን አቋርጦ ሲሻገር የሰው ልጅ ቆሞ እያደንቀው ይመለከታል፤ እርሱ ሲንቀሳቀስ ሁሉም ነገር ይንቀጠቀጣል። የኔ ልጅ የፍጥረትን ትኩረትን ይስባል፡፡” አለቻት፡፡

ሌሎች መቅስፈት በሚመስል ጊዜ ነገራቸው ሲቀየርና የተሳካላቸው ሲመስልሽ በነሱ አትቅኝ፤ እምነትሽም አይጥፋ፤ በፍጹምም ተስፋ አትቁረጭ፤ ምክንያቱም የአንቺም ጽንስ የሚወለድበት ጊዜ ይመጣል።

ምንም ጊዜ ወስዶ የማይመጣ ቢመስልም የተሻለው መምጣቱ የማይቀር ነው፤ እናም ሲመጣ ሰዎችን ሁሉ የሚያነጋግርና የሚያስደንቅ ይሆናል፤ የዘገየው የተሻለ ስለሆነ ነውና የአንቺን ጉዞ ከሌላ ከማንኛውም ሰው ጋር አታነፃፅሪ።

ትልቅ ሁሌም ትልቅ ነው!
ትልቅ ነገር ትልቅ ዋጋ አለው!