የዛሬ 36 ዓመት ገደማ ከኮሌጅ ተመርቃ የ 22 ዓመት ልጅ እያለች “WJZ-TV” የሚባል የቴሌቪዥን ጣብያ ውስጥ በዜና አንባቢነት ተቀጥራ ትሰራ ነበር ። በወቅቱ በዛ ቴሌቭዥን ጣብያ በእድሜ ትንሿና ብቸኛዋ ጥቁር አሜሪካዊ ዜና አንባቢ ነበረች። ነገር ግን “….ለቴሌቪዥን የሚሆን መልክ የለሽም! ብዙም አትመስጪም! ተመልካች ሳቢም አይደለሽም! ፀጉርሽ ሉጫ አይደለም! ብቃትሽም ቢሆን እምብዛም ነው! በተደጋጋሚ ዜና ስታነቢ ቃላቶችን በተሳሳተ መንገድ ስትጠሪ ታዝበናል! “ብለው የቴሌቪዥን ጣብያው አመራሮች በመጀመርያ ከስራ ዝቅ (Demote) እንድትደረግ ያደርጉና ከዛም ከስራ ገበታዋ ያባርሯታል ።

በሚገባ ውሃ ፣ መብራትና መፀዳጃ ቤት እንኳን የሌለው ቤት ውስጥ ያደገችው ፣ ነጮችን በቤት ሰራተኝነት ከሚያገለግሉት አያቷ ጋር ልጅነቷን ያሳለፈችው ፣ እጅግ በጣም ስኬታማ ከሆነች የቤት ሰራተኛ (Maid) ነው የምትሆነው ተብሎ በቤተሰቦቿ የተተነበየላት ፣ በገዛ አጎቷና በዘመዶቿ ወዳጆች አካላዊ እና ፆታዊ ጥቃቶች የደረሰባት ፣ ገና በ 9 ዓመቷ በአሰቃቂ ሁኔታ የተደፈረችው ፣ ድጋሚ በ 14 ዓመቷ ተደፍራ ፣ አርግዛ ከዛም ልጇ “premature” ስለነበረ የሞተባት ፣ በግፍ አትችይም ተብላ ከቴሌቪዥን ዜና አንባቢነት የተባረረችው “Oprah Winfrey” ዛሬ ላይ “የቴሌቪዥን ቶክ ሾዋ ንግስት (Queen of television talk shows)” በሚል ቅፅል ስም ነው የምትጠራው አባዬ! የሷን ያህል በቲቪ Talk show ዘርፍ ስኬታማ የሆነ ማንም ሰው የለም። ለወደፊትም ይኖራል ማለት ከባድ ነው! ምክንያቱም “ሚልየነር” ሳይሆን “ቢልየነር” ሆናበታለች! ሴትየዋ 2.7 ቢልዮን ዶላር ብቻዋን ታወጣለች! አሜሪካ ብትሄድ ብቸኛዋ ጥቁር ሴት ቢልዮነር እሷ ናት ።

በ “University of Pennsylvania” “History 298: Oprah Winfrey, the Tycoon” የሚባል ኮርስ እንደሚሰጥ ታውቃለህ አባዬ? ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “ኦፕራ እንዴት ሃብታም ልትሆን ቻለች?” የሚለውን ይመረምራሉ ስልህ! በነገራችን ላይ በጣም የምትታወቅበት “The Oprah Winfrey Show” ለ 25 ዓመታት ከ “September 8, 1986” እስከ “May 25, 2011” የተላለፈ ሲሆን በአሜርካ የቴሌቪዥን ታሪክ ትልቅ የተመልካች “rating” ያለው እንደሱ የለም! “Oprah” የመጀመርያዋ የራሷ ሾው አዘጋጅም ፕሮዲውሰርም መሆን የቻለች ተዓምረኛ ሴት ናት ። ዛሬ ላይ በተለያዩ የቴሌቪዥን ጣብያዎች ላይ የምታያቸው የ “Talk show” ፕሮግራሞች የተገለበጡት ከሷ እና ከ “David Letterman” ነው! ሁሉም በሚቻል ደረጃ!

ለ 25 ዓመታት የተላለፈው “The Oprah Winfrey Show” “4561” ክፍሎች (Episodes) አሉት! Who does that? እነዚህን ክፍሎች አውርደህ በቀን እንኳን አንድ ክፍል ብታይ በ 12 አመት ነው የምትጨርሰው እንዳትሞክረው “Oprah Winfrey” ድንቅ ፣ ጠንካራ ፣ ብርቱ ፣ ዐርዓያ ፣ ተምሳሌት ፣ ጀግና ፣ ሃብታምና ለብዙ ዜጎች ስራ ፈጣሪ በመሆንዋ በ 2013 የሃገሪቷን ከፍተኛ የክብር ሽልማት(Presidential Medal of Freedom) በወቅቱ የሃገሪቷ ፕሬዝዳንት ከነበሩት “Barack Obama” የተቀበለች ሴት ናት ። በነገራችን ላይ ምን ያህል ተፅህኖ ፈጣሪ እንደሆነች የምታውቀው በ 2008 የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 1 ሚልዮን የሚሆኑ መራጮች ድምፃቸውን ለ “Barack Obama” እንዲሰጡ ያደረገች ሰው መሆንዋን ስታውቅ ነው ።