”በአንድ ወቅት አንድ ሰው ?ፈረስ እየጋለበ ሳለ የሚመለከተው ሌላኛው ሰው ጋላቢውን ‘ወዴት እየሄድክ ነው?’ ብሎ ይጠይቀዋል። ያም ሰው ‘ፈረሱን ጠይቀው ብሎ ይመልስለታል።”
<ምንጭ: ‘Bad boys for life’ ፊልም>

ፈረስ በሰው ይጋለባል። ይሄ ማለት ታዲያ ሰውየው ከላይ ተቀምጦ ፈረሱም ሰውየውን በላዩ ላይ አስቀምጦ ነው። ታዲያ ያ ፈረስ በሚሮጥበትም ጊዜ በጋላቢው መሪነት ነው። ነገር ግን ፈረሱ ራሱን የሚመራና ከበላዩ በተቀመጠው ሰው የማይመራ ከሆነ ትክክለኛ አካሄድ ነው ልንል አንችልም!

?? እኛ የምናውቀውን ስሜታችንን በትክክል ካልመራነው ራሳችንን ለስሜታችን ከተውንና በስሜታችን ከተመራን ግን ‘ፈረሱን ጠይቀው’ አይነት ኑሮ ነው ምንኖረው…

?? አእምሮአችንን መሪ ካላደረግን ልናውቀው ሲገባ ያላወቅነው ስሜታችን ህይወታችንን ወዳልሆነ መንገድ ይወስደዋል።

?? ሠው ከመሆናችን ውስጥ አንዱ ልዩ ነገር ስሜታችን በአምሮአችን ግዛት ውስጥ እንዲሆን ተደርገን መፈጠራችንም ነው።

?? ስለዚህ… ሁልጊዜም ህይወታችን በማን መሪነት ውስጥ እንዳለ እንወቅ፤ የመድረሻው ማማር ከመሪው መስተካከል ጋር እንደሚገናኝ እናስተውል!… ባልሄድንበት አንደርስም…

?? ፈጣሪ አእምሮ በመስጠቱ ውስጥ አካሄዳችንን ለማስተካከል እድል መቸሩን እንረዳ።

❔ማን እየመራን ነው?

?? በዋናነት የስሜት ምሪት እንደሚያጠፋው ሁሉ ደግሞ የአእምሮም በፈጣሪ አለመመራት ሌላ #ትልቅ_ጥፋት ነው።

?? ፈጣሪ ከአእምሮአችንም በላይ ነውና ምንግዜም ለእኛ የሚበጀውን ያውቃል፤ እንዲመራን ስንፈቅድም መድረሻችንን ከማሳመር አልፈን ለሌሎች መድረሻ ማማር ምክንያት እንሆናለን።

✔️ እኛ ስሜታችንን እንምራው እንጂ ስሜታችን እኛን አይምራን!!!