ምን የምትፈራው ነገር አለ? ሕልምሕን እንዳታሳካ ምን የሚያስፈራህ ነገር አለ? ራስህን ለመቀየር ስታስብ ምን ያስፈራሀል? ብዙ ሰዎችን “በሕይወታችሁ ምን የሚያስፈራችሁ ነገር አለ?’ ብዬ ስጠይቃቸው፡ “እኔ ምንም ነገር አልፈራም!” ብለው ይመልሱልኛል።

አንተስ የሚያስፈራህ ነገር ምንድን ነው? ወይስ እንደ አብዛኞቹ ሰዎች ምንም የምትፈራው ነገር የለህም? ብዙ ሰዎች ፍራቻ ምን እንደሆነና እንዴት እንደሚሰራ አያውቁም፡ በመሆኑም በሕይወታቸው የሚያስፈራ ነገር ሲመጣ ይደነግጣሉ፣ ፍራቻቸውን እንዴት እንደሚያሸንፉም አያውቁም። አንተም ፍራቻን እንዴት እንደምታሸንፍ ካላወክ ልትደነግጥ ትችላለህ። ፍራቻ ምን እንደሆነ እንዴት እንደሚሰራ ከየት እንደመጣ ለመረዳት፣ ሕልምህን ለማሳከትና ሕይወትህን ለመቀየር በጣም ቀላል ይሆንልሃል። አሁን ፍራቻ ምን እንደሆነ ለመረዳት የሚያግዙህን ጥያቄዎች ልጥውይቅህ።

ትልቅ ህልም አለህ ? ሕልምህ ምንድን ነው? ሕልምህ ተሳክቷል? ሕልምህን እንዳታሳካ የከለከለህ ነገር ምንድን ነው ? ሕልምህን እንዳታሳካ የከለከለህ ነገር ፍራቻ ይሆን?

ታድያ ፍራቻህን ማሸነፍ ትፈልጋልለህ? በዚህ ዓለም፣ “ደፋር” የሚባሉት ስለማይፈሩ አይደለም። ሰዎች “ደፋር” የሚባሉት ፍራቻቸውን ሰለሚያሸንፉት ነው። ሰው ደፋር የሚባለው ሳይፈራ ሲቀር ሳይሆን፣ ፍራቻው በውስጡ እያለ መሆን ያለበትን የሚሆንና መስራት ያለበትን የሚሰራ ሲሆን ነው። አነተም በሕይወትህ እያደግክ ስትሄድ፣ የተለያዩ ፍራቻዎች ያጋጥሙሃል። ታድያ እነዚህን ፍራቻዎች እንደ ኮምፓስ ወደ እድገትህ መሄጃ ተጠቀምባቸው። ደፈርና ጀግና በመሆን ፣ በሕይወትህ የሚያጋጥሙህን ፍራቻዎች ለይተህ አጥንተህ ተረዳቸውና ፊት ለፊት ገጥመህ በመጋፈጥ አሸንፋቸው።

ከዳዊት ድሪምስ ትልቅ ህልም አለኝ መጽሐፍ የተወሰደ።