የዛሬዋን ጠዋት ለማየት የትልንቱን ምሽት ማሳለፍ ግዴታ ነው ፡፡ ዛሬ እንዲነጋ ትላንት መጨለሙ የተፈጥሮ መስተጋብር ነው ፡፡መጨለሙን ጠልተን ንጋቱን የቱንም ያህል ብንፈልገው ሳይጨልም ሊነጋ አይችልም በከባድ ችግሮች ውስጥ ያላችሁ ሁሉ ይህን አስተውሉ ሳይጨልም እንደማይነጋው ሁሉ ከጨለመም መንጋቱ አይቀርም ተራራ መስሎ ከፊትህ የተደቀነው ችግር፣ በልባህ ውስጥ ያለው ሀዘን በሀሳብ ያለው ተስፋ መቁረጥ እነዚህ ሁሉ ያንተ መጨረሻ ሳይሆኑ የጅማሬዎችህ መጨረሻ ናቸው ፡፡ ስኬት መጨረሻ (መድረሻ) ሳይሆን መዳረሻህ ላይ ለመድረስ የምታደርገው የሂወት ትንቅንቅ ነው፡፡
መዳረሻህ ላይ ለመድረስ ህልምህ እውን ሲሆን ለማየት፣ ነገህን ብሩህ ለማድረግ፣ ለማሸነፍ የዛሬ ያሁን ፈተናዎችን ማለፍ አቅምህ እስከሚችል እስከ መጨረሻው ህቅታ ድረስ መታገል ግዴታ ነው፡፡በህወታችሁ የማይነጋ የሚመስል ለሊት እያሳለፈችሁ ላላችሁ እህትና ወንድሞቼ ይሄ የማይነጋ የሚመስለው ለሊት ችግሮቻችሁ፣ ሸክሞቻችሁ፣ እያሳለፋችሁት ያላችሁት ህመም እነዚህ ሁሉ የቀጣይ ደረጃ ምልክቶች ናቸው ፡፡ ለማሸነፍ ምን ያህል ቅርብ እንደሆናችሁ ማሳያ ነው፡፡የወደቃችሁት ለማሸነፍ ስላልተፈጠራችሁ አይደለም ፡፡ ወደዚህ ምድር ራቁቱን ባዶውን የመጣ አለም፡፡ ችግሮችን እና ህመሞችን እያሳለፋችሁ ያላችሁት ስለተገባችሁ ሳይሆን ትጠነክሩ ዘንድ ግዴታ ስለሆነ ነው፡፡ከጠነከራችሁ ፣በይቻላል ካመናችሁ፣ እያሸነፋችሁ ባይሆንም በራሳችሁ ከተማመናችሁ የማይነጋ የሚመስለው ነግቶ፣ የማያልፍ የሚመስለው አልፎ፣ የተከዘው ገፃችሁ እንደ አበባ ፈክቶ የተሻለ ነገን እንደምታዩ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡ሊነጋ ሲል ይጨልማል ጨልሞ አይቀርም ዳግም ይነጋል !
ይህም አልፎ ድሮ ብለህ ታወራለህ ቀን ያልፍና ትፅናናለህ !